Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ አሜሪካ ምዕራባውያኑን በማስተባበር ወደ ዩክሬን የምትልከውን የጦር መሣሪያ አቅርቦት ካላቆመች እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ወደ ዩክሬን የምትልከውን የጦር መሣሪያ አቅርቦት የማታቆም ከሆነ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች፡፡

የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ራያብኮቭ አሜሪካ ወደ ዩክሬን የጦር መሳሪያዎች እየላከች መሆኑን ሀገራቸው እንደደረሰችበት አስታውቀዋል፡፡

ሰርጌይ ራያብኮቭ ÷አሜሪካ ወደ ዩክሬን ከምትልከው የጦር መሣሪያ አቅርቦት በተጨማሪ እንግሊዝን ጨምሮ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት በአሜሪካ አስተባባሪነት የጦር መሣሪያ አቅርቦት መላካቸውን ነው የገለጹት፡፡

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ቻናል ዋን” በተሰኘው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ÷ “አሜሪካ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራትን በማስተባበር የመሣሪያ አቅርቦት ወደ ዩክሬን በገፍ እያስገባች መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ አካሄድም አደገኛ አካሄድ መሆኑን ለአሜሪካ ነግረን አስጠንቅቀናል፤ ከዚህ በኋላም አሜሪካ ከድርጊቷ የማትታቀብ ከሆነ አቅርቦቱን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ ዩክሬን ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረች ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ በሩሲያ ላይ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦችን በመጣል፥ የሩሲያን ኢኮኖሚ ለማድቀቅ እና በሀገሪቷ ያለውን የገንዘብ ዝውውር በማዳከም ከገንዘብ ተቋማት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማስተጓጎል ስትሰራ መቆየቷን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version