Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ለሚያገናኘው የአርጆ‐ጉደቱ‐ጅርማ‐ሶጌ መንገድ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን በዲጋ ወረዳ የአርጆ ጉደቱ ጅርማ ሶጌ 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ነው በጋራ የተቀመጠው
መንገዱ 392 ሚሊየን ብር የተመደበለት ሲሆን፥ ወጪውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደሚሸፍነው ተገልጿል።

መንገዱ ሲጠናቀቅ የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ይበልጥ ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

መንገዱ በአስፋልት ደረጃ እንደሚገነባም ተገልጿል።

 

በትዝታ ደሳለኝ

Exit mobile version