Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት አሸባሪዎችንና ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ሰነድ ተፈራረሙ።
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት “ሠላማዊ እና ደህንነቷ የተረጋገጠ አፍሪካን ” ለመፍጠር በድንበር፣ በሳይበር፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ዙሪያ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በወጣቶችና ሥራ አጥነት በሌሎችም ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የወታደራዊ መረጃ ፎረም በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ታንዛኒያና ዩጋንዳ ተሳትፈዋል።
በቀጠናው ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩት የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት ኢትዮጵያ ለፎረሙ መሳካት ላደረገችው አስተዋጾኦ አመስግነዋል።
ቀጣዩን የምክክር መድረክ በኡጋንዳ እንደሚካሄድ የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version