Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኮምቦልቻ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን÷ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን በማሳደግ አብሮነታችንን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
መሰል ዝግጅቶችም ማህበረሰቡን በማስተሳሰርና ያለው ለሌለው እንዲረዳ በማድረግ በኩል ሚናው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙ ምእመናንም ወቅቱ መረዳዳት የሚገባን በመሆኑ ሀሉም ሊተጋገዝ ይገባል ብለዋል።
Exit mobile version