Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በግንባታ ላይ ያለውን አዲሱን የኢቢሲ ሕንፃ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሸጎሌ የሚገኘው እና በግንባታ ላይ ያለውን አዲሱን የኢቢሲ (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ) ሕንፃ ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአሠራር ምቹ ያልሆነው የኢቢሲ የአሁኑ ሕንፃ በአዲስ እንደሚቀየር ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር ውይይት ባደረጉት ወቅት ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለትም በሸጎሌ የሚገኘው አዲሱ የኢቢሲ ሕንፃ ያለበትን ሂደት ተመልክተዋል።
አዲሱ የኢቢሲ ሕንፃ ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ሥራ የሚጀምር ሲሆን ሕንፃው ዘመናዊ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ስቱዲዮች ይኖሩታል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ይህም ተቋሙ በይዘት እና አቀራረብ የተሻለ ሆኖ ለመውጣት እያደረገ ያለውን ጥረት ይበልጥ እንደሚያሳድግለት ታምኖበታል።
Exit mobile version