Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪምየርሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ደረጃውን ያሻሻለበትን ውጤት አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በ19ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሸሏል፡፡

ከደቂቃዎች በፊት በተካሄደው ጨዋታ አንጋፋው ተጫዋች ጋዲሳ መብራቴ እና ሄኖክ አየለ የድሬዳዋን የአሸናፊነት ጎል ሲያሰቆጥሩ ዳዊት በፍቃዱ ብቸኛዋን የጅማ አባ ጅፋር ጎል አስቆጥሯል፡፡

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎም ድሬዳዋ ከተማ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ 2 ደረጃን በማሻሻል በ 20 ነጥብ በጎል ክፍያ ተበልጦ ከመከላከያ የእግር ኳስ ቡድን ጋር 12ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

የ19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ መካሄዳቸውን የቀጠሉ ሲሆን ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version