Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሆስፒታሉ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ተሾመ ÷ ሆስፒታሉ ህክምናውን እየሰጠ ያለው ከ”ሂማሊያን ካታራክትና ላይፍ ፎር ዘ ዎርልድ” ከተሰኙ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር መሆኑን ተናግረዋል።

ከሚያዝያ 7 እስከ 13 ቀን 2014 ዓም ድረስ ለአንድ ሳምንት በሚሰጠው ህክምና ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡

ህክምናውን ለማግኘት ለሚመጡ ሰዎች ከአገልግሎቱ በተጨማሪ የትራንስፖርት፣ የምግብና የአልጋ ወጪ በነጻ የሚሸፈንላቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ ከጋሞ፣ ከጎፋ፣ ከደቡብ ኦሞ፣ ከኮንሶና፣ ከሃዲያ ዞኖች ጨምሮ ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልልና ከደራሼ፣ ከአሌ፣ ከቡርጂና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ለሚመጡ ሰዎች አገልግሎቱ እየተሰጠ ሲሆን÷ባለፉት አራት ቀናትም በተደረገ ህክምና 800 የሚሆኑ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version