Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
በአሜሪካ ዳላስ የኢትዮጵያ ግብረ-ሀይል ከ16 ሚሊየን 900 ሺህ ብር በላይ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በፍራንክፈርት ከ561 ሺህ ብር በላይ እና ሀዲያ ዓለም አቀፍ በዳያስፖራ ማህበር 221 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የዳያስፖራ ተወካዮች የተሰበሰበውን ገንዘብ ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ አስረክበዋል።
በቀጣይም የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተወካዮቹ ገንዘቡን ባስረከቡበት ወቅት አረጋግጠዋል።
የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ዳያስፖራው አገሩንና ወገኑን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።
ዳያስፖራው እያደረገ ያለውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ኮሚሽነሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version