Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከሩሲያና ዩክሬን መሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከሩሲያና ዩክሬን መሪዎች ጋር ሊወያዩ ነው።
 
ጉተሬዝ በነገው እለት ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
 
ከዚህ ባለፈም ከሁለት ቀናት በኋላ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጋር የሚወያዩ ይሆናል።
 
በውይይታቸው ለጦርነቱ እልባት መስጠት በሚቻልበት አግባብ ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
Exit mobile version