Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሰሜን ሸዋ ዞን አንዲት እናት 4 ልጆችን ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ በሙከጡሪ ሆስፒታል አንዲት እናት አራት ልጆችን ተገላገለች፡፡
በምጥ ከተወለዱት አራት ሕጻናት ውስጥ ሦስቱ ወንዶች ሲሆኑ÷ አንደኛዋ ሴት መሆኗን የሆስፒታሉ የተቀናጀ የማህጸንና ድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያ ዶክተር ሃብታሙ ቱሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናገረዋል፡፡
ሕፃናቱ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን÷ በአሁኑ ሰዓት በምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ባለሙያው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሕጻናቱ መወለድ ከነበረባቸው ጊዜ ቀደም ብላው እንደተወለዱ እና ክብደታቸውም ሁለቱ ሕጻናት 1 ኪሎ ግራም ሲሆን÷ አንደኛው 1 ነጥብ 2 ኪሎ ግራም እንዲሁም ሌላኛው 1 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም እንደሆነ ዶክተር ሃብታሙ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version