Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶክተር ሊያ ታደሰ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጤና ሚኒስትር ጂያን ምባንዳ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በሁለቱ አገራት በጤናው ዘርፍ ጠንካራ አጋርነት መፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተለይም ለህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነት እና ምላሽ መስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በትኩረት መወያየታቸውን ዶክተር ሊያ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

Exit mobile version