Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ከነገ በስቲያ ሰኞ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ከነገ በስቲያ ሰኞ ሚያዝያ 24 ይከበራል ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለፀው ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን ባለመታየቷ በዓሉ ከነገ በስቲያ ሰኞ ይከበራል።

የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡስማን አደም በዓሉ ከነገ በስቲያ ሰኞ እንደሚከበር ተረጋግጧል ብለዋል።

ምክር ቤቱም ህዝበ ሙስሊሙም በዓሉን ሲያከብር በተለመደው የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል ሊሆን እንደሚገባ ገልጿል።

ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነትን፣ አብሮነትን እንዲሁም ሀገራዊነትን በማጠናከር እና ለሰላም ቅድሚያ በመሥጠት ሊሆን እንደሚገባም ነው ያሳሳበው።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

Exit mobile version