Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዴንማርክ የልማትና ትብብር ሚኒስትር ፍሊሚንግ ሞለር ሞርቲንሰን የተመራ ልዑክ ጎዴ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴንማርክ የልማትና ትብብር ሚኒስትር ፍሊሚንግ ሞለር ሞርቲንሰን የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጎዴ ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ጎዴ ዑጋዝ ሜራድ ሊይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ልዑኩ ድርቁ በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን እና የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ እንዲሁም ለድርቁ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ እና በመሠረተ ልማት አቅርቦት ላይ ድጋፍ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
Exit mobile version