Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለአትሌቲክስ ቡድኑ ሽልማት እና እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዶሃ ለተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ልዑካን የሽልማትና የምስጋና መርሃ ግብር ተካሄደ።

ቡድኑ በውድድሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማምጣት ከዓለም 8ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጣነቅል።

ምሽቱንም በኤሊያና ሆቴል የእውቅናና ሽልማት ስነ ስርአት ተካሂዷል።

በውድድሩ ለተሳተፈው ቡድን በሽልማት መልክ ከ2 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት ተሰጥቶታል።

የወርቅ ሜዳሊያ ያመጡ 40 ሺህ ብር፣ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ያመጡት ደግሞ እያንዳንዳቸው በቅደም ተከተል 30 ሺህ እና 20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Exit mobile version