Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ800 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ ጥንታዊ የእጅ ጽሑፎችን የያዘ ሙዚየም ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ800 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ ጥንታዊ ጽሑፎችን የያዘ ሙዚየም በሐረር ከተማ ተመረቀ፡፡
ሙዚየሙ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች እና አመራሮች በተገኙበት ነው ተመርቆ የተከፈተው፡፡
በሐረር ከተማ እየተከበረ የሚገኘው የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር አካል በመሆን የተመረቀው ሙዚየሙ÷ ከ800 እስከ 900 ዓመታት ያስቆጠሩ ጥንታዊ በዕጅ የተፃፉ ጽሑፎችን የያዘ መሆኑን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ሙዚየሙ የኢትዮጵያን በተለይም በሐረር ከተማ የሚገኙ እረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ የባህል እና የታሪክ መረጃዎችን አደራጅቶና ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
Exit mobile version