Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህወሓት ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ከተሞች የውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች መስጫ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ከሚሴና ወረኢሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች 19 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ያሰባሰቡት እና ከተቋሙ በጀት በመመደብ የተገኘ ሲሆን÷ ድጋፉም የተለያዩ የውሀ አገልግሎት ቁሳቁሶች፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የውሃ ፓምፕ፣ ኮምፒዩተርና ፕሪንተሮች እንዲሁም ፓወር ኬብል እና ሌሎች መሣሪያዎችን ያካተተ ነው።

የኮምቦልቻ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ተወካይ ኃላፊ አቶ ኑረዲን ኢማም፥ ድጋፉ አገልግሎቱን በአግባቡ ለመስጠትና ንፁህ የመጠጥ ውሀ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተርና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰባሳቢ ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው ፥ የውሃ ተቋማትን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመደገፍ ያለመ ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአንድነት ናሁሰናይ

Exit mobile version