አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አትሌት ፀሐይ ገመቹ በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን በተካሄደው የግመሽ ማራቶን ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፈች፡፡
አትሌቷ የሊዝበንን ግማሽ ማራቶን ርቀት 1 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጎይተይቶም ገብረ ስላሴ 1 ሰዓት ከ06 ደቂቃ 45 ሴኮንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡