Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዋልያዎቹ የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ግንቦት 25 ቀን ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚያደርግባቸው ቀናት ይፋ ሆነዋል፡፡
የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች በዚህ ወር መካሄድ የሚጀምሩ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ 2 ጨዋታዎችን የምታደርግበት ቀናት ታውቀዋል፡፡
በምድብ መ ከግብፅ፣ ጊኒ እና ማላዊ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ÷ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ ከማላዊ ብሄራዊ ቡድን ጋር ግንቦት 25 ቀን 2014 ታደርጋለች፡፡
ሁለተኛ ጨዋታዋን ደግሞ ግንቦት 29 ከግብፅ ጋር የምታደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version