Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ ትሳተፋለች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ ትሳተፋለች፡፡
በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትሮች እንዲሁም በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን የያዘችው አትሌት ለተሰንበት በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ እንደምትሳተፍ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።
አትሌቷ ጥቅምት 2021 ላይ ባደረገችው የቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ውድድር የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን በመስበር ማሸነፏ ይታወሳል፡፡
ይህንን ድል ባስመዘገበችበት ቫሌንሺያ ከተማ ደግሞ በፈረንጆቹ 2022 በማራቶን ትሳተፋለች፡፡
Exit mobile version