Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምዕራብ ጎጃም ዞን በኢንቨስትመንት አማራጮች እና መሰናክል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ለኢንቨስትመንት ዘርፍ መሰናክል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።

በመድረኩ በዞኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሳተፉ ባለሀብቶች እና የክልል እና የዞን ባለስልጣናት ተሳትፈዋል።

አካባቢው የኢንቨስትመንት አቅም እንዳለው እና መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት ቢሆንም የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ዝቅተኛ መሆኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ ተናግረዋል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ በአከባቢው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ እርምጃ ወስዶ ዘርፉን ማነቃቃት መሆኑን ጠቁመዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው÷ በክልሉ በርካታ የኢንቨስትመንት ሀብቶች እንዳሉና ዞኑም ቀዳሚ መሆኑን አመላክተዋል።

በፀጋዬ ወንድወሰን

Exit mobile version