Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የደስታ መግለጫ አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሆነው ድጋሚ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፈ።

የሶማሊያ ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።

ትናንት በተካሄደው ምርጫ የመጨረሻ ድምፅ አሰጣጥ ሞሀመድ ስልጣን ላይ የነበሩትን መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆን በማሸነፍ ነው የተመረጡት።

Exit mobile version