Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፑንት ላንድ ልዑካን በሶማሌ ክልል በቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ትግበራ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፑንት ላንድ የመጡ ልዑካን በሶማሌ ክልል በዓለም ባንክ እና በሌሎችም ተቋማት በሚደገፈው የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ትግበራ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው።
በክልሉ በዚህ ፕሮጀክት 36 ወረዳዎች የታቀፉ ሲሆን÷የማህበረሰብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከመገንባት ጀምሮ የእንስሳት መኖ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ተከናውነዋል።
የልኡካን ቡድን አባላቱ በኢትዮጵያ ካለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኘውን የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ፕሮጀክቶቹ እየተተገበሩ ባሉባቸው ቦታዎች ላይ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል።
በይስማው አደራው
Exit mobile version