Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፍትህ ሚኒስትሩ እየተከናወነ ባለው የዘርፉ ማሻሻያ ዙሪያ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ በተደረጉ የህግ ማሻሻያዎች እና በሚዲያ ነጻነት ላይ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በግጭት ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ሃይል ስራ ላይ መምከራቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version