Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘው አገራዊ መድረክ በድሬዳዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስለ ኢትዮጵያ” በሚል ሁለተኛው አገራዊ መድረክ ዛሬ በድሬዳዋተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልና እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እና ከየ ዘርፉ የተውጣጡ ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡
ስለ ኢትዮጵያ እናምርት! በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው መድረኩ÷ ኢትዮጵያን ከ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ጀምሮ እስካሁን ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በመጎብኘት ተጀምሯል።
የዛሬው መድረክ በኢንዱስትሪ ልማትና በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ስላለው መልካም እድል፣ ተግዳሮትና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አዘጋጅነት የሚካሄደው አገራዊ መድረኩ በአስራ አንድ ከተሞች የሚካሄድ ሲሆን÷ የመጀመሪያው በጅግጅጋ በቅርቡ መካሄዱ ይታወሳል።
በታሪኩ ለገሰ
Exit mobile version