Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል።

ከባህር ዳር ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደረገው ሲዳማ ቡና ጨዋታውን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ጊት ጋትኩት፣ ይገዙ ቦጋለ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ የሲዳማን የድል ጎሎች አስቆጥረዋል።

አሊ ሱሌማን ደግሞ የባህር ዳር ከተማን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።

ቀትር ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ሃዲያ ሆሳዕና ከወልቂጤ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ጌታነህ ከበደ ለወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ተስፋዬ አለባቸው ለሃዲያ ሆሳዕና ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
Exit mobile version