Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም ዋንጫ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2022ቱ የኳታር የዓለም እግር ኳስ ውድድር አስቀድሞ በተለያዩ ሀገራት ለእይታ የሚቀርበው የዓለም ዋንጫ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ብራዚላዊው የባርሴሎና የቀድሞ የቀኝ መስመር ተከላካይ በጁሊያኖ ቤሌቲ ዋንጫውን ይዞ አዲስ አበባ ገብቷል።

ዋንጫው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የባህልና ስፖርት የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።

ነገ ግንቦት 17 ቀን በመስቀል አደባባይ ለዕይታ ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡

ዋንጫው በአፍሪካ ከሚቆይባቸው ዘጠኝ አገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗም ተገልጿል፡፡

በበአካል ዳንኤል

Exit mobile version