Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህልና ዙምባራ ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህልና ዙምባራ ፌስቲቫል በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በፌስቲቫሉ የፖናል ውይይቶችና ባህላዊ ትርዒቶች ቀርበዋል ።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች በህዝቦች መካከል ትውውቅና አንድነት ለማምጣት መሰል መርሃግብሮች ያስፈልጋሉ ብለዋል።
ፌስቲቫሉ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለውም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የብዝሃነት መልክ ያላት ናት ያሉት ተሳታፊዎቹ ብዝሃነትን በአዎንታዊ መንገድ ለሀገር ግንባታ ለመጠቀም እንደሚያስችልን አመላክተዋል።
የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በጋራ ባዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል የፓናል ውይይቶችና ጉብኝቶች ይካሄዳሉ ተብሏል።
በአፈወርቅ እያዩ
Exit mobile version