Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የካራማራ ድል 42ኛ ዓመት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው መሪ ዚያድባሬ ጦር በ1969 ዓ.ም ኢትዮጵያን ለመውረር የሞከረበትና ድል የተደረገበት የካራማራ ድል 42ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት ተከበረ።

በዓሉ አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮ ኩባ የወዳጅነት ፓርክ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በአከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ የጦር ጄኔራሎች፣ መኮንኖች እና ወታደሮች እንዲሁም ወጣቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የሀገርን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በተደረገው ጦርነት የተሰው ዜጎችን ለማስታወስ በተሰራው ሐውልት ላይ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተካሄዷል።

Exit mobile version