Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቱርክ የንግድ ሚኒስትር ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቱርክ ንግድ ሚኒስትር መህመት ሙስ ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ አገራቱ ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የቱርክ የንግድ ሚኒስትር መህመት ሙስ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ኢስታንቡል መግባታቸው ይታወሳል፡፡
በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አደም መሀመድ በኢስታንቡል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል ማድረጋቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version