Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ካቀረቡ ሩሲያ አዳዲስ ኢላማዎችን ለመምታት ትገደዳለች – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን “አሜሪካም ሆነች ሌሎች ምእራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ማቅረብ ከጀመሩ አዳዲስ ኢላማዎችን ለመምታት እንገደዳለን ሲሉ” አስጠንቅቀዋል።
እንደዚህ ዓይነት ሚሳኤሎች ለዩክሬን የሚቀርቡ ከሆነ የሩሲያ አጸፋ ከባድ ይሆናል፣ ከዚህ በፊት ያልመታናቸውን ኢላማዎች ለመምታት እንገደዳለን ብለዋል ፕሬዚዳንት ፑቲን ለአንድ የቴሌቪሽን ጣቢያ በሰጡት ቃለምልልስ ፡፡
ምዕራባዊያን ለዩክሬን የሚያደርጉት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ጦርነቱን ለማጓተት ያለመ ነው ሲሉም ፕሬዚዳንት ፑቲን ምእራባዊያኑን ኮንነዋል፡፡
አሜሪካ እና ሌሎች ምእራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤል ካቀረቡ ሩሲያ ስለምትመታቸው አዳዲስ ኢላማዎች ዝርዝር ግን ፕሬዚዳንት ፑቲን ያሉት ነገር አለመኖሩን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version