Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ ከነገ ጀምሮ የሚተገበር የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን ገለፀ፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው የተደረገው አለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህም በመዲናዋ በሚገኙ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ይርጋለም ብርሀኔ ናቸው።
የነዳጅ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት ዋጋ ላይ ከነገ ጀምሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 3 ብር 50 ሳንቲም ጭማሪ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮው አስታውቋል።
በዚህም በሚድ ባስ 0.50 ሳንቲም እስከ 2.00 ብር የተጨመረ ሲሆን በሚኒ ባስ 0.50 እስከ 3.50 ተጨምሯል።
ህብረተሰቡ ከሰኔ አንድ ጀምሮ ተግባራዊ ከሚደረገው የክፍያ ታሪፍ በላይ የሚጠይቁ ህገ ወጥ አካላትን ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Exit mobile version