Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ታንዛኒያ በስደት የሚኖሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታንዛኒያ መንግስት በውጪ አገራት ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ የአገሪቱ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በታንዛኒያ ዋነኛ ተፎካካሪ ፓርቲ የሆነው ቻድማ÷ በአገሪቱ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ በውጪ አገራት ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጠይቋል፡፡
ፓርቲው ጥሪውን ያቀረበው የታንዛኒያ መንግስት በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ እና ዛቻ ምክንያት በውጪ አገራት በስደት የሚኖሩ የተፎካካሪ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡
የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ÷ በመንግስት እና በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት በስደት ከሚኖሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን አስታውቋል፡፡
የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ወደ አገራቸው ሲመለሱም አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና እንደሚሰጣቸው ሚኒስቴሩ ማስገንዘቡን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
ስለሆነም በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት በውጪ አገራት ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ነው የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ ያቀረበው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version