Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፀረ-ህዝብ ኃይሎችን በማጥፋት በኩል ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ውጤታማ ስራ እየሠራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፀረ-ህዝብ ኃይሎችን በማጥፋት በኩል ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ውጤታማ ስራዎችን እየሠራ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኦሮሚያ ከምዕራብ አርሲ፣ ከቦረና፣ ከምዕራብና ምስራቅ ጉጅ፣ ከባሌና ከአርሲ ዞኖች እንዲሁም ከደቡብ እና ከሲዳማ ክልል ዞኖች ከተውጣጡ የፀጥታና የአስተዳደር አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እንደገለፁት የሠላም ዕጦት የዜጎችን ኑሮ የሚያናጋ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሀገር ዕድገት ፀር ነው።

የህዝብ ሰላም በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ ሁሉም የፀጥታ እና የአስተዳደር አካላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በተጠናከረ መንገድ ተቀናጅቶ በቀጣይነት መስራት እንዳለባቸው መናገራቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሀገርን ሠላምና የህዝብ ተረጋግቶ የመኖር ዋስትናን የሚፈታተኑ ፅንፈኛ ኃይሎችን ህልውና ለማክሠም እርስ በእርሳቸው በመደጋገፍ ከሠራዊቱ ጋር ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version