Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ ሉዓላዊነቷን እንድታስከብር ቻይና ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ገለፀች

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሩሲያ ሉዓላዊነቷን እንድታስከብር ሀገራቸው ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ሺፒንግ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሀገራቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የስልክ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ዢ ቻይና በሞስኮ ሉዓላዊነት እና ደህንነት ዙሪያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ለፕሬዚዳንት ፑቲን ገልፀውላቸዋል፡፡

የሞስኮን የተለያዩ ፍላጎቶች ጨምሮ ሉዓላዊነቷ እና ደህንነቷ እንዲጠበቅ ቻይና ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ ናት ሲሉ መግለፃቸውን ሺንዋን ጠቅሶ አረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version