Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

1ሺህ 126 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 126 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመለሱት ውስጥ ስድስቱ ሕጻናት መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ38 ሺህ 853 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version