Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና የሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ በጋራ ለመስራት በሚያስሉ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና የሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ከሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል÷ ሜጀር ጀነራል አብዲ ሀሰን ሙሀመድ እና ከልዑካቸው ጋር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሪፎርሙ ባከናወናቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ሁለቱ አገራት በቀጣይ በመረጃ ልውውጥ፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመከላከልና በአቅም ግንባታ በኩል በጋራ ለመስራት እና የሶማሊያ ብሔራዊ ፖሊስ ኦፊሰሮችን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል÷ ለአህጉራዊ ሰላም ሌሎች የአፍሪካ አገራትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ተሞክሮ በመውሰድ በጋራ መደራጀትና መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version