Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከ44 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተዘጋጁ

አዲ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዘንድሮው ክረምት በሚካሄደው የአረጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከ44 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ሙሉ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ብርሃኑ ኢትቻ እንደገለጹት÷ በክልሉ በ4ኛው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከ44 ሚሊየን 900 በላይ ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል፡፡
በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሚተከሉት ችግኞች ለደን ልማት፣ ለደንና ጥምር እርሻ፣ ለብዝሃ ሕይወት ጥበቃ እንዲሁም ለሆልቲ ካልቸርና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚሰጡ መሆናቸውንም ነው ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን የገለጹት፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ መርሐ ግብሩም÷ የመተከልና ካማሽ ዞኖችን ጨምሮ በክልሉ አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው ሁሉም አካባቢዎች እንደሚከናወንም ገልጸዋል፡፡
እስከ አሁን ባለው መረጃም 1 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚጠጋ ጉድጓድ ተቆፍሮ ዝግጁ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ባለፈው ክረምት ከተተከሉት ችግኞች መካከል የፀደቁት በቁጥር ከ67 በመቶ በላይ እንደሆነም
ነው የጠቆሙት።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version