Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።

ፕሪሚየር ሊጉ በመጠናቀቂያ ቀኑ በተካሄዱ ሶስት ጨዋታዎች ሰባት ጎሎች ተቆጥረውበታል።

ቀደም ብሎ ረፋድ ላይ በተካሄደ ጨዋታ መከላከያ ጅማ አባጅፋርን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ምሳ ሰአት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ሲዳማ ቡና ከሃዲያ ሆሳዕና ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

በጨዋታው ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው የሲዳማ ቡናው ይገዙ ቦጋለ በ16 ጎሎች የሊጉ ከፍተኛ ጎል አግብ በመሆን ጨርሷል።

10 ሰአት ላይ በተካሄደውና የዘንድሮው ውድድር መዝጊያ በነበረው መርሐ ግብር ደግሞ ባህር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች የዘንድሮው የሊጉ አሸናፊና ሶስተኛው ወራጅ ክለብ የተለየ ሲሆን፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮንነቱን ማረጋገጡ የሚታወስ ነው።

አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ጅማ አባጅፋር እና ሰበታ ከተማን ተከትሎ ሶስተኛው ወራጅ ክለብ ሆኗል።

የፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ጎልም በዛሬው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡናው አብነት ደምሴ ተመዝግባለች።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version