Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለቻን ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ 23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ ሱዳን ጋር የቻን ማጣሪያ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።
በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንደሚጠብቀው ይታወቃል።
ሐምሌ 15 እና 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች÷ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።
ከግብ ጠባቂነት÷ ፋሲል ገብረ ሚካኤል፣ በረከት አማረ እና አላዛር ማርቆስ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከተከላካዮችም÷ ሱሌይማን ሀሚድ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባየህ፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን የሱፍ እና ጊት ጋትኩት በጥሪው ተካተዋል፡፡
ጥሪ የተደረገላቸው አማካዮች÷ ጋቶች ፓኖም፣ከነዓን ማርክነህ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣፣በዛብህ መለዮ፣ በረከት ደስታ፣ አማኑኤል ዮሐንስ እና መስዑድ መሐመድ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከአጥቂዎች ደግሞ÷ ቸርነት ጉግሳ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ዳዋ ሆቴሳ እና ብሩክ በየነ ጥሪ እንደተደረገላቸው ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም÷ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version