Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ፉክክር ሪሺ ሱናክ አብላጫውን ድምጽ አገኙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር የድምጽ አሰጣጥ ሂደት የሀገሪቱ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ አብላጫውን ድምጽ ማግኘታቸው ተገለጸ፡፡

የድምጽ ቆጠራው ውጤት እንዳመላከተው ሱናክ 88 ድምፅ በማግኘት ከተፎካካሪዎቻቸው የላቁ ሲሆን የንግድ ሚኒስትሩ ፔኒ ሞርዳውንት 67 ድምጽ አግኝተዋል።

እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ 50 ድምፅ በማግኘት የቀድሞውን የገንዘብ ሚኒስትር ተገዳድረዋቸዋል ነው የተባለው።

ቀሪዎቹ ሦስት እጩዎች እያንዳንዳቸው ከ40 የማይበልጥ ድምፅ አግኝተዋልም ነው የተባለው።

በመጀመሪያው ዙር ፉክክር የገንዘብ ሚኒስትሩ ናዲም ዛሃዊ እና ጄረሚ ሃንት አነስተኛ ድምጽ በማግኘት ከቀጣዩ ፉክክር ውጭ መሆናቸው ታውቋል።

ስድስቱ ተፎካካሪዎችም ሁለት የመጨረሻ ዙር ተፎካካሪዎች እስከሚቀሩ ድረስ እንደሚወዳደሩ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version