Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ እና ዩክሬን በውይይት ሠላም እንዲያሰፍኑ ቻይና ጠየቀች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሹ ጁቲንግ፥ ሩሲያ እና ዩክሬን ጥቅማቸውን ባስጠበቀ መልኩ በመካከላቸው ለቆየው ውዝግብ ዕልባት እንዲሰጡ ቻይና መጠየቋን ገልጸዋል።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጸሐፊ ጃኔት ዬለን ሩሲያ የነዳጅ ዋጋ በምትቀንስበት አግባብ ላይ ከቻይናው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ዩ ሂ የበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።

ከውይይቱ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄም ሩሲያ እና ዩክሬን በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በሰላም እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረቧን ገልጸዋል።

ቻይና ከዚህ ቀደም ሀገራቱ ልዩነቶቻቸውን በሰላም እንዲፈቱ ጥሪ ስታቀርብ መቆየቷን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል።

Exit mobile version