Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በተሁለደሬ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 129 ፋልኮን ሽጉጥ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 129 ፋልኮን ሽጉጥ ተያዘ፡፡
 
ህገ ወጥ ሽጉጡ መነሻውን ጎንደር ከተማ አድርጎ ከሚሴ ከተማ ለማድረስ በነዳጅ ታንከር ውስጥ ሲጓጓዝ የደቡብ ወሎ ዞን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች መምሪያ ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ እና የተሁለደሬ ወረዳ ፖሊስ በጋራ በመተባበር በሰሩት ስራ ነው የተያዘው፡፡
 
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተደረገበት እንደሚገኝም ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version