Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዮርዳኖስ ዓባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዮርዳኖስ ዓባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን ክለቡ አስታወቀ፡፡
ድሬዳዋ ከተማ ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ÷ አሰልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይ ለአንድ ዓመት ክለቡን እንዲያሰለጥን ተሹሟል፡፡
ዮርዳኖስ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ወደ አሰልጣኝነቱ በመግባት በናሽናል ሲሚንት እና ድሬ ዳዋ ፖሊስ የአሰልጣኝነት ሕይወትን የጀመረ ሲሆን÷ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመከላከያ በምክትል አሰልጣኝነት ሲሠራ መቆየቱን ሶከር ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version