Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዶክተር ሙሉቀን ሃብቱ ያለመከሰ መብት እንዲነሳ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክር ቤቱ አባል የሆኑት የዶክተር ሙሉቀን ሃብቱ ያለመከሰ የህግ ከለላ መብት እንዲነሳ ወሰነ።
 
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡
 
የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
 
ያለመከሰስ መብት ይነሳልን ጥያቄው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ የቀረበ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
ጉባኤው በቀረበለት አስቸኳይ አጀንዳ መሰረትም ዶክተር ሙሉቀን የምክር ቤት አባል በመሆናቸው ምክንያት ያላቸውን ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ መወሰኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃያመላክታል፡፡
Exit mobile version