Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ጥሩ አፈጻጸም ያሳዩ ባለሀብቶችን እንደሚደግፍ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው ጥሩ አፈፃፀም ያሳዩ ባለሀብቶችን ለማበረታታት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦድሪን በድሪ ገለጹ፡፡
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተደድር ኦርዲን በድሪ በሆቴልና ቱሪዝም እና የማህበራዊ አገልግሎት ለመስጠት በግንባታ ላይ የሚገኙና በግንባታ ላይ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን ጎብኝተዋል፡፡
የግንባታዎቹ አፈፃፀም 60 በመቶ መድረሱን የገለፁት ባለሀብቶች ከዚህ የበለጠ ግንባታቸውን አጠናቀው ወደስራ ለመግባት ግን የሲሚንቶ እጥረት እና የግንባታ ግብአቶች ዋጋ መጨመር እንቅፋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡
በግንባታ ላይ ያሉት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት ለዜጎች የስራ እድልን ከመፍጠርና የክልሉን ቱሪዝም ከማሳደግ አኳያ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም የክልሉ መንግስት የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማሳደግ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ባለሃብቶቹ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ እንደሚያግዝ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ በተቃራኒው የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደውና መሬት ተረክበው ወደ ስራው ያልገቡ ባለሃብቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ባሻገር ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
በቲያ ኑሬ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version