Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር የአውሮፕላኖችን እግር መለዋወጥ የሚያስችል ስምምነት ፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ማረፊያ እግሮች መለዋወጥ የሚያስችል ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱ÷ አየር መንገዱ በቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ላይ የሚደረጉ የ “ላንዲንግ ጊር” ጥገናዎችን የበለጠ ቀልጣፋ በማድረግ አውሮፕላኑን በአጭር ጊዜ ለበረራ ብቁ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት÷ ይህ ስምምነት አየር መንገዳችን የቦይንግ ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ወደ አገልግሎት ባስገባበት 10ኛ ዓመት ላይ የተደረገ ነው፡፡
ይህም ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ያለንን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ማሳያ ነው ማለታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version