Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ዋግኽምራ የሰብአዊ እርዳታ ሟጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰብአዊ እርዳታ ሟጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ፥ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በዋግኽምራ ዞን በሚገኙት አበርገሌ፣ ፃግብጂ እና ዝቋላ ወረዳዎች እየተጓጓዙ መሆኑን ገልጿል፡፡

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከሌሎች አደጋዎች የከፋ መሆኑን የገለፀው ተቋሙ ፥ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶች መቀጠል እንዳለባቸውም አስገንዝቧል፡፡

Exit mobile version