Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡
በዚህም መሠረት÷
1. አቶ ቸንኮት ቾት – የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ቡን ዊው – የክልሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ኮንግ ጆክ – የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ቶክ ፕሊፕ – የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል በጉባዔውስነ ምግባር ችግር ምክንያት ሦስት ዳኞች ከሥራቸው እንዲሰናበቱ እና ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ሲደረግ የ19 ዳኞች ሹመት በቀጣይ ጉባዔ እንዲታይ ተወስኗል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version