Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ባይደን ስትራቴጂክ የጦር መሳሪያን በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋሽንግተን አዲሱን የስትራቴጂክ የጦር መሳሪያ ቅነሳ እና ቁጥጥር ማዕቀፍ በተመለከተ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ገለጸች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአሥረኛው ከፀረ- የጦር መሳሪያ መስፋፋት ስምምነት የግምገማ ጉባኤ ቀደም ብሎ በሰጡት መግለጫ አገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ባይደን በመግለጫቸው፥ “ዛሬ የኔ አስተዳደር በ2026 ጊዜው የሚያልቀውን ስምምነት የሚተካ አዲስ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ማዕቀፍ ላይ ለመደራደር ዝግጁ ነው” ብለዋል።

ቻይናም በአዲሱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥጥር ስምምነት ላይ ድርድር ማድረግ አለባት ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ነገር ግን ድርድሩ በቅን ልቡና የሚሰራ ፈቃደኛ አጋር ይሻል ሲሉም ተናግረዋል።

ምንጭ፡- አርቲ

Exit mobile version