Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዩክሬንን እህል የጫነችው መርከብ ቱርክ ወደብ ደረሰች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መርከቧ በትናንትናው ዕለት በቦስፎረስ ባህር ወሽመጥ አቅራቢያ ቱርክ ግዛትመድረሷ ተነግሯል።
ራዞኒ የተሰኘችው መርከብ ከ26 ሺህ ቶን በላይ በቆሎ ወደ ሊባኖስ እና ትሪፖሊ ታደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
የሩሲያ እና የዩክሬን ባለስልጣናትን ያካተተ ቡድን መርከቧ ወደ ሊባኖስ የምታደርገውን ጉዞ ለማስቀጠል ጭነቱን ዛሬ ይመረምራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ጭነቱ የተጫነው በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የእህል እና የማዳበሪያ የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ከስምምነት ከተደረሰ በኋላ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
መርከቧ ከኦዴሳ ወደብ ከትናንት በስቲያ መነሳቷን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version